
"እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን" የሐዋ. ሥራ 6፥4
Upcoming Event

ከላይ የተጠቀሰውን ኃይለ ቃል የተናገሩት አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ናቸው። የተናገሩበት ምክንያት የማኅበረ ካህናት እና ማኅበረ ምዕመናን የአገልግሎት ድርሻቸውን በማሳወቅ ለእግዚአብሔር መንግሥት እንዲተጉ ለማድረግ ነው።
በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በካናዳ የካልጋሪ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ተተኪ አገልጋዮችን ማፍራት እና የልማት እንቅስቃሴን ጨምሮ የዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በማከናወን ላይ ይገኛል። ሰውን ከማልማት፣ ማለትም በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሕዝቡን በመሰብሰብ ለንስሐና ለሥጋ ወደሙ በማብቃት፣ ሰውና እግዚአብሔር እንዲገናኙ ማድረግ በመቻሉ በሁለት ዓመታት ውስጥ ሕዝቡን በማስተባበር የሁለገብ ሕንጻችንን ግንባታ ለማጠናቀቅ የመጨረሻ ሥራ ላይ እንገኛለን።
በአጠቃላይ የካልጋሪ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል እየሰጠ ያለው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለብዙዎች ኢትዮጵያንና ኤርትራውያን ወገኖቻችን መጽናኛ ተስፋቸው ሁኖ እንዲኖር ወደፊት ከማኅበረ ካህናቱ፣ ከሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ቦርድ እና ከማኅበረ ምዕመናን ወምዕመናት ጋር በመሆን የታቀዱ ዕቅዶቻችንን በተሰጠን ጊዜ ሰርተን ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ እንችል የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን አማላጅነት የመልአኩ ተራዳኢነት አይለየን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!
ቆሞስ መላክ ገነት አባ ኪዳነ ማርያም
አስተዳዳሪ
"But we will give ourselves continually to prayer, and to the ministry of the word." Acts 6:4
The above powerful words were spoken by our holy fathers, the Apostles, to make known the shared responsibility of both the priesthood and the congregation in serving the Kingdom of God.
Based on this same foundation, our church is actively engaged in nurturing new clergy and carrying out a wide range of development and service activities. By helping people grow spiritually, the Church strives to bring all into communion with God. Through this blessed mission, and with the cooperation of the faithful over the past two years, we have now reached the final stage of completing the construction of our two-story church building.
In general, the spiritual and community services provided by Calgary Debre Mihret St. Gabriel Cathedral have become a source of comfort and hope for many of our Ethiopian and Eritrean faithful. Going forward, with the continued support of the clergy, the spiritual administrative board, and the congregation, we will carry out our planned projects diligently, so that we may hand over a lasting legacy to the next generation.
May the goodness of God, the intercession of our Holy Mother, and the protection of the Archangel Gabriel never depart from us.
Glory be to God, Amen!
Melake Genet Komos Aba Kidnemariam
Administrator
Regular Service
Every Sunday : Holy Liturgy
Every Friday: Friday Prayer and Sermon:
5:30 pm to 7:30 pm.
.jpeg)

.jpeg)
.jpeg)
.jpeg)



